በአዲስ አበባ የሚገኘው የአቡነ ጴጥሮስ ሀውልትሊፈርስ ነው

ህዳር ፲፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:- በአዲስ አበባ የሚገኘው የአቡነ ጴጥሮስ ሀውልትሊፈርስ ነው:፡ ዛሬ በሸገር ኤፍ ኤምላይ ቀርበው መግለጫ የሰጡት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሀላፌ እንዳሉት ከባቡር ስራ ጋር በተያያዘ የአቡነ ጴጥሮስ ሀውልት ይነሳል::

ሆኖም መነሳቱ በጊዜዊነት ነው ሀዲዱ ከተሰራ በሆላ ወደቦታው ይመለሳል ብለዋል::

የኢሳት ምንጮች ከፕሮጀክት መሀንዲሶች አካባቢ የተገኘን መረጃ ጠቅሰው እንደገለጡት የሀዲዱ ዲዛይን ላይ ለሚነሳው የአቡነ ጴጥሮስ ሀውልት ላይ ቦታ የለም እናም ሀውልቱ እንደፈረሰ የመቅረቱእድል የሰፋ ነው ሲሉ ገልጠዋል:፡ በተያያዘ መረጃ በዲዛይን ላይ የአጼ ሚኒሊክ ሀውልት ተመሳሳይ እጣ ፈንታ ሊገጥመው እንደሚችል ታውቆል:: መንግስት ጊዚያዊ ነው ቢልም ዲዛይኑ የሚያረጋግጠው ግን ሀውልቶቹ እስከወዲያኛውም ወደቦታቸው እንደማይመለሱ ነው::

ከፍተኛ ተቃውሞ የቀረበበትና በሲኖዶስ እንዲፈርስ የተወሰነው የአቡነ ጳውሎስ ሀውልት ቆሞ የታላቁ አርበኛና መስዋእት አቡነ ጴጥሮስ ሀውልት ሊፈርሱ ነው መባሉ በእርግጥ አነጋጋሪ ሆኖል።