በአሜሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የሻማ ማብራት ሥነ-ሥርዐት ሊያደርጉ ነው

ት ዜና:- በአሜሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በእስር ላይ የሚገኙ ጋዜጠኞችና የፖለቲካ ድርጅት መሪዎች እንዲፈቱ ለመጠየቅ በኋይት ሀውስ ፊት ለፊት የሻማ  ማብራት ሥነ-ሥርዐት ሊያደርጉ ነው::

ማርች ፎር ፍሪደም ለኢሳት በላከው መግለጫ ላይ እንዳመለከተው ኢትዮጵያኑ ኖቪምበር 6 በኋይት ሀውስ ለፊት ከ6ፒኤም ጀምሮ የሻማ ማብራት ሥነ-ሥርዐት በማድረግ በእስር ላይ የሚገኙት ጋዜጠኞችና ፖለቲከኞች እንዲፈቱና የኦባማ አስተዳዳር በመለስ ዜናዊ አገዛዝ ላይ ጫና እንዲያሳርፉ ይጥይቃሉ።

በስነስርአቱ ላይ ወ/ት ብርቱካን ሚዴቅሳ እንደሚገኙም ማርች ፎር ፍሪደም አስታውቋል።በቅርቡ  ተመሳሳይ የሻማ ማብራት ሥነ-ሥርዐት በዚሁ በኋይት ሀውስ ፊት ለፊት መካሄዱ ይታወሳል።