በስዊዘርላንድ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጽህፈት ቤት ፊት ለፊት ደማቅ ሰላማዊ ሰልፍ አደረጉ

ህዳር 4 ቀን 2004 ዓ/ም

 

ኢሳት ዜና:-በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን በዛሬው እለት ፣ ኖቬምበር 14 ፣ 2011 ባደረጉት የተቃውሞ ሰልፍ ፣ የመለስ መንግስት በንጹሀን ዜጎች ላይ እየወሰደ ያለውን እመቃ አውግዘዋል፣ በእስር ላይ የሚገኙት የፖለቲካ መሪዎችና ጋዜጠኞች ደግሞ እንዲፈቱ ጠይቀዋል።

የመለስ መንግስት በርካታ ጋዜጠኞችንና የፖለቲካ ድርጅት መሪዎችን በሽብር ስም ማሰሩ ይታወቃል።