በምዕራብ ጎጃም በፍኖተሰላም ዙሪያ ወረዳ ጫካ የገቡ ወጣቶችን ለመያዝ ወታደሮች ወደ አካባቢው መንቀሳቀሳቸው ታወቀ

ጥቅምት ፲፰ (አሥራ ስምንት ) ቀን ፳፻ / ኢሳት ዜና :- ራሳቸውን አደራጅተው ወደ ገጠር በመውጣት በወታደሮች ላይ ጥቃት ሲሰነዝሩ የሰነበቱ ወጣቶችን ለመያዝ በሚል በሶስት ኦራል መኪኖች የተጫኑ ወታደሮች ወደ አካባቢው አምርተዋል። ባለፈው ሳምንት ከፍተኛ የተኩስ ለውውጥ ይሰማ እንደነበር የገለጹት የአካባቢው ምንጮች፣ ዛሬም የተኩስ ድምጽ ይሰማ እንደነበር ተናግረዋል። ይህንኑ ተከትሎ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ወጣቶች ተይዘዋል። ወታደሮች ህዝቡን እያወከቡት መሆኑንም ነዋሪዎች ገልጸዋል።