ስዊድናውያን ጋዜጠኞቹን በህገ-ወጥ መንገድ እንዲገቡ የላከው ተቋም ይከሰስ ተባለ

የካቲት 29 ቀን 2004 ዓ/ም

ኢሳት ዜና:- “ስዊድናውያን ጋዜጠኞቹን ወደ አገራችን በህገ-ወጥ መንገድ እንዲገቡ የላከው ተቋም ቢከሰስ ፤በሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ ሊቀጣ ይችላል”ሲሉ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጋዜጠኝነትና የኮሙኒኬሽን ዲን ተናገሩ።

በህወሀት አባልነት የሚጠቀሱትና  በዩኒቨርሲቲው የጋዜጠኝነትና የኮሙኒኬሽን ፋኩሊቲ ዲን የሆኑት  ዶክተር ገብረመድህን ስምዖን ይህን ያሉት፤በጉዳዩ ዙሪያ ለመንግስት ጋዜጠኞች በሰጡት አስተያዬት ነው።

ስዊድናውያኑን ጋዜጠኞች ለማስፈታት እየተደረገ ያለው ዲፕሎማሲያዊ ጥረት መፍትሔ ወደሚያገኝበት ደረጃ ላይ መድረሱ በተነገረ ማግስት፤ዶክተር ገብረመድህን ፦”ጋዜጠኞቹን የላካቸው ተቋም ቢከሰስ ገንዘብ እንደሚገኝ” ሀሳብ መስጠታቸው ብዙዎችን አስገርሟል።

የዶክተር ገብረመድህንን አስተያዬት በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ያነበቡ ታዛቢዎች፦”ሰውዬው የተመረቁት፤ በቢዝነስ አድሚንስትሬሽን ነው? ወይስ በጋዜጠኝነት?” ሲሉ ተሳልቀዋል።

___________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________

ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.

ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide