ሰብአዊ መብቶች ጉባኤ በደቡብ ክልል በርካታ አርሶአደሮች መታሰራቸውን ገለጠ

መጋቢት ፳፩ (ሃያ አንድ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-በቀድሞ አጠራሩ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ጉባኤ ፣ ከገዢው ፓርቲ በደረሰበት አፈና ሰብአዊ መብቶች ጉባኤ የሚል ስያሜ አገኘው ኢሰመጉ በ118ኛ እና 119ኛ  በከፋ ዞን በገዋታ ወረዳና ዙሪያ ከ1950 ዓም ጀምሮ የሚኖሩ የኦሮሞ ተወላጆች ልጆቻቸው በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው እንዲማሩና በማህበር እንዲደራጁ እንዲፈቀድላቸው በመጠየቃቸው ከ20 የማያንሱ  ሰዎች ታስረዋል። በዚሁ ጥያቄ የተነሳም 33 ሰዎች ቤት ንበረታቸው ንብረታቸው ተቃጥሎባቸው ከቦታቸው እንዲፈናቀሉ ተደርጓል።

ሰመጉ ቦታው ድረስ በመሄድ ለማጣራት እንደቻለው መንግስት እና የክልሉ መንግስታት የሚፈጸመውን የሰብአዊ መብት ጥሰት ለማስቆም እርምጃ ሲወስዱ አልታየም።

በ119ኛ ልዩ መግለጫው ደግሞ ሰመጉ በአርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ የሚኖሩ የላንቴ ቀበሌ ነዋሪዎች የአካባቢው ባለስልጣናት የህዝቡን መሬት እየተከፋፈሉ ቤቶችን መስራታቸውን በመቃወማቸው ፣ 33 ሰዎችን ለምን ተቃውሞ አሰማችሁ በሚል ምክንያት አስረዋቸዋል። ከእነዚህም መካከል ከህዝቡ ጋር በመሆን የባለስልጣናቱን ድርጊት የተቃወሙት አቶ ሉቃስ ገላና አቶ ደስታ ዳና የተባሉ የግብርና  ሰራተኞች ተይዘው ታስረዋል።

በላንቴ ቀበሌ ያለው ሁኔታ እጅግ አሳሳቢ በመሆኑ መንግስት አስቸኳኢ መፍትሄ መስጠት እንደሚገባው ሰመጉ አሳስበኦል።

በደቡብ ክልል በጉራጌ ዞን ቸሀ ወረዳ ጋሶሬና ካራቻ ቀበሌ  ከ200 በላይ የቤተሰብ አባላት የያዙ 19 አባዎራዎች መሬታቸው ተነጥቆ ለባለሀብት መሰጠቱን ቢቃወሙም የተረፋቸው ግን እስርና መስፈራራት ነው። የመቃብር ቦታዎች ሳይቀሩ ለባለሀብቱ በመሰጠቱ ነዋሪዎች የቀብር ቦታ ማጣታቸውም በሪፖርቱ ተመልክቷል።

ኢሳመጉ ላለፉት 19 አመታት በርካታ የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን ሲያጋልጥ በመቆየቱ ከመንግስት ተደጋጋሚ ተጽእኖ ደርሶበታል። በባንክ ያለው ገንዘቡም እስካሁን እንደታገደበት መሆኑ ይታወቃል።

___________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________

ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.

ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide