ሰሞኑን በጦርነት ወሬ ሲታመሱ የቆዩት ደቡብና ሰሜን ሱዳን አንዱ በሌላው ላይ ጦርነት ላለመጫር ተስማሙ

የካቲት 3 ቀን 2004 ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-ሁለቱ አገሮች ስምምነቱን የፈረሙት በቀድሞው የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንት በታቦ ምቤኬ አደራዳሪነት በአዲስ አበባ ነው።

ሁለቱ አገሮች አንዱ የሌላውን ሉአላዊነት ለማክበር ተስማምተዋል፤ አላስፈላጊ ከሆነ ፕሮፓጋንዳም ራሳቸውን እንደሚያቅቡ ፈርመዋል ሲሉ ታቦ ምቤኪ ተናግረዋል።

በቅርቡ ከነዳጅ ዘይት ጋር በተያያዘ የተነሳው አለመግባባት ለድርድር አለመቅረቡም ተመልክቷል። ደቡብ ሱዳን በኢትዮጵያ በኩል አልፎ ጅቡቲ የሚደርስ የነዳጅ ቧንቧ ለመዘርጋት ስምምነት መፈረሙዋ ይታወሳል።