ሰላም ባስ ጋራዥ ላይ የደረሰውን ጥቃት ተከትሎ አካባቢው በፖሊስ እየተጠበቀ ነው

(ኢሳት ዜና –ሐምሌ 14/2009)የሕዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ/ሕወሃት/ንብረት በሆነው ሰላም ባስ ጋራዥ ላይ ጥቃት የተፈጸመው ሐሙስ ምሽት ላይ ነበር።

ስፍራውም ሳሪስ አካባቢ በቀለበት መንገድ መስመር ላይ እንደሆነም ተመልክቷል።

በፖሊስ በተከበበው የሰላም ባስ ጋራዥ ውስጥ መርማሪ ባለሙያዎች መሳሪያዎችን ይዘው የፍንዳታውን ሁኔታ ሲያጠኑ እንደነበር የሚገልጹት ምንጮች ስለጉዳቱ መጠን ለማወቅ አለመቻላቸውን ገልጸዋል።

የህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ ንብረት የሆነው ሰላም ባስ ከኢትዮጵያ የመንግስት ባንኮች አላግባብ በተወሰደ ገንዘብ የተቋቋመና በዘርፋ ላይ የተመሰረተ የሕወሃት ኩባንያ ነው በሚል ትችት ሲቀርብበት መቆየቱ ይታወሳል።

በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች ሲንቀሳቀስም ለጥቃት የተጋለጠ መሆኑ ይታወቃል።

በኦሮሚያ ክልል አመጽ የመሰባበር አደጋ ሲያጋጥመው በአማራ ክልል አምጽ ደግሞ አንድ አውቶቡስ ሙሉ በሙሉ ተቃጥሏል።

በዚህም የተነሳ ለተወሰኑ ጊዜያት ወደ ኦሮሚያና ወደ አማራ ክልል የሚያደርገው ጉዞ ተገቶ መቆየቱ ይታወሳል።