ሞዛምቢክ 24 ኢትዮጵያዊያን ስደተኞችን ወደ አገራቸው መለሰች

ግንቦት ፩ ( አንድ ) ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ሕገወጥ ቪዛ አስመትተው ከአዲስ አበባ ወደ ሞዛምቢኳ መዲና ማፑቶ የገቡ 24 ኢትዮጵያዊያን ስደተኞችን ወደ አገራቸው እንዲመለሱ ማድረጋቸውን የአገሪቱ ባለስልጣናት አስታወቁ።
ከኢትዮጵያዊያኑ ስደተኞች በተጨማሪም 11 የባንግላዲሽ ዜጎችም በተመሳሳይ ሁኔታ በመግባታቸው እነሱም ወደ ትውልድ አገራቸው ተልከዋል። ኢትዮጵያዊያኑ ስደተኞች በማፑቶ አውራጃ በማቫሊ ድንበር አቆራርጠው ወደ ሞዛምቢክ መግባታቸውንም ባለስልጣኑ አክለው ገልጸዋል።
ባለፈው ሚያዚያ ወርም በተመሳሳይ ሁኔታ13 ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች፣ አንድ ሕንዳዊ፣ አንድ የባንግላዴሽ ዜጋና አንድ ናይጀሪያዊ ከሞዛምቢክ ወደ ትውልድ አገራቸው መመለሳቸውን ዴሊኔሽን አስታውሷል።