መለስ በመድረክ ውስጥ ያልታሰሩ የሽብርተኛ ድርጅቶች አባላት አሉ ብለው የተናገሩትን የመድረኩ መሪ አጣጣሉት

የካቲት 1 ቀን 2004 ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-አቶ መለስ ዜናዊ 99 ነጥብ ስድስት በመቶ በራሳቸው የፓርቲ አባላት በተያዘው ፓርላማ ፊት ቀርበው ባደረጉት ንግግር በመድረክ ውስጥ ለፍርድ ቤት በቂ የሆነ ማስረጃ ያላገኘንባቸው የአሸባሪ ድርጅቶች አባላት አሉ በማለት መናገራቸው ይታወቃል።

የመድረኩ ሊቀመንበር የሆኑት ዶ/ር ሞጋ ፍሪሳ በበኩላቸው አቶ መለስ ዜናዊ በሰው ህሊና ውስጥ ያለውን ነገር እንዴት እንደሚያውቁ አላውቅም ሲሉ መልሰዋል::

አቶ መለስ ዜናዊ በሽብረተኝነት የተከሰሱ ሰዎች ጥፋተኞች ነን ብለው የሚያምኑ ከሆነ፣ በምህረት እንለቃቸዋለን ብለው መናገራቸው ይታወሳል።

ይሁን እንጅ በእስር ላይ የሚገኙትና በ14 ፣ 17 እና በ19 አመታት እንዲቀጡ የተፈረደባቸው ጸሀፊና መምህርት ርእዮት አለሙ፣ ጋዜጠኛ ውብሸት ታየ፣ አቶ ዘሪሁን ገብረእግዚአብሄርና ወ/ት ሂሩት ክፍሌ ዬይቅርታ ጥያቄ ያቅርቡ አያቅርቡ  አልታወቀም።

ሁለቱ የስዊድን ጋዜጠኞች በህገወጥ መንገድ ወደ አገር መግባታቸውን በማመን ይቅርታ ቢጠይቁም፣ አሸባሪዎች ወይም የሽብርተኞች ተባባሪዎች ግን አይደለንም በማለት ገልጠዋል።